የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መተዳደሪያ መመሪያ 1001 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መተዳደሪያ መመሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በሚኖርበት፤ በሚማርበት በሚሰራበት አካባቢ በስፖርት እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ለዚህም አላማ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲስፋፉና እንዲጠበቁ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በየአካባቢው በብዛትና በጥራት መኖርና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት የህብረተሰቡን በተለይም የወጣቱን ጤንነት ለመጠበቅ፣ አካል ለመገንባት፣ አዕምሮ በማበልጸግ ለሃገር እድገት አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ለማስቻልና ስፖርቱ ለታሰበለት ዓላማና ግብ እንዲውል ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚቋቋምበትን፣ የሚተዳደሩበትን ፣ ቁጥጥር የሚደረግበትን፣ ሕጋዊ ጥበቃ የሚያገኙበትን ግልፅ፣ ውጤታማ፣ የተቀናጀና ተጠያቂነት ባለበት ተቋማዊ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡ ዓላማ :-የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በበላይነት በማስተዳደር ፣ደህንነታቸውን በማስጠበቅ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በእኩልነትና በፍታሃዊነት አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል፡፡